Sunday, November 18, 2018

እስቲ “ፍትህ ለኢትዮጵያ” እንበል!


... 1871 በፈረንሣዊው ዩጂን ፖቲየ የተደረሰውና የግራ-ዘመሞች (በዋናነት የሶሻሊስቶች) መዝሙር የሆነውንኢንተርናሲዮናልበልጅነታችን በትምህርት ቤት የዘመርን ሁሉ እናስታውሰዋለን፡፡ በግጥሙ ውስጥ ካሉት ስንኞች መካከል፡-
ፍትህ በሚገባ ይበየናል፤
ሻል ያለ ዓለምም ይታያል፡፡
--
የሚሉ ይገኙበታል፡፡
የሶሻሊስታዊያንና የግራ-ዘመሞች የፍትህበሚገባ የመበየንምኞት ሙሉ በሙሉ ዕውን ሳይሆን ቀርቶ፣ በምትኩ ፍትህ-አልባነት መገለጫቸው ሆኖ እስከ ኮሙኒዝም ፍጻሜ ድረስ ቀጥሏል፡፡ አሁንም ቢሆን፣ በግራ ዘመም የፖለቲካ አራማጅ ኃይሎች የሚመሩ በርካታ አገራት ፍትህ-አልባነት ዋነኛ መለያቸው እንደሆነ ቀጥሏል፡፡ 
አገራችን ኢትዮጵያም፣ በተለይ 1966 አብዮት አንስቶፍትህ፣ እኩልነት፣ ነጻነትየሚሉ መፈክሮች ሲስተጋቡባት የኖረች ብትሆንም፣ ቃልና ተግባር ያልተገናኙባት፣ እንዲያውም በተቃራኒው፣ ከቀደሙት ዘመናት በከፋ መንገድ እነዚህ መብቶች የተረገጡባት ምድር ሆናለች። ለመብቶቹ መረጋገጥ በርካታ ዓመታትን የወሰዱና ከፍተኛ መስዋዕትነት ያስከፈሉ ትግሎች ተካሂደውጨቋኝየተባሉ አስተዳደሮች ቢወገዱም፣ በምትካቸው የመጡት አሸናፊዎች ከመሻል ይልቅ እየባሱ፣ ከመምራት ይልቅ እየገዙና የጭካኔ መንገዳቸውንም እያከፉ ለሌላ ዙር አመጽና ትግል በር ሲከፍቱ፣ በዚህም ትግል እነርሱም ከወንበራቸው በመፈንገል አዙሪቱን አስቀጥለውታል፡፡ 
በእያንዳንዱ የአገዛዝና የወንበር ለውጥ ማግሥት፣ የተለያዩ የሕዝብ ጥያቄዎች፣ የተዳፈኑበትን አመድ እያራገፉ ወደ አደባባይ መውጣታቸው የተለመደ ነው፡፡ ዜጎች በተለያዩ አደረጃጀቶችአሉንየሚሏቸውን ጥያቄዎች ይዘውፍትህ ይሰጠንበማለት በተለያዩ መንገዶች ድምጻቸውን ያሰማሉ፡፡ ጥያቄዎቻቸው ምንም ያህል የተለያዩ ቢሆኑም፣ ማጠንጠኛቸው በዋናነትፍትህ አጣንየሚል ነው፡፡
ይህ የፍትህ ጥያቄ እጦት ጉዳይ መሬት የረገጠና በተጨባጭ የሚታይ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለያየ ደረጃ ሊገለጽ የሚችል ነው፤ ስለሆነም የፍትህ ጥያቄዎች እዚህም አዚያም ጎላ ብለው ቢደመጡ የሚገርም አይደለም። ለጥያቄዎቹም ምላሽ መስጠት በዋናነት ከመንግሥት የሚጠበቅ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡
በዚህ አግባብ ከዛሬ ሦስት ዓመታት በፊት በአገራችን የተለያዩ ክፍሎች የሕዝብ ብሶትን መነሻ አድርገው የተቀጣጠሉ ተቃውሞዎች በመንግሥት አመራር ላይ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ለውጥ እንዲፈጠር መንስኤ መሆናቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ በዚህ ለውጥ ባለፉት ሰባት ወራትይሆናሉተብለው ያልተጠበቁ መሻሻሎች በፍጥነት እያየን ነው፡፡ ይህ በራሱ መልካም ጅምር ሆኖ ወደፊትም በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ፍላጎት መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ከዚህ መልካም ጅማሮና ከተገኙ ውጤቶች ጎን ለጎን፣ በርካታ ያልተፈቱና ሕዝቡ አሁንም እንዲፈቱለት የሚጠይቃቸው በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ኅብረተሰቡም በተለያዩ መንገዶች ጥያቄውን ማቅረቡን አላቋረጠም፡፡
እነዚህን ጥያቄዎች ለማቅረብ በሰላማዊ ሰልፍ፣ በማኅበራዊ ሚዲያዎችና በሌሎችም መንገዶች ከሚስተጋቡ መፈክሮች መካከልፍትህ ለእከሌ፣ፍትህ ለእነ እንቶኔ፣” “ፍትህ ለዚህ ሕዝብ….” የሚለው ዋነኛው ነው፡፡ ጥያቄዎቹ በዚህ መልክ መነሳታቸው ምንም ክፋት ባይኖረውም፣እንደኔ እምነት፣ ሁሉንም የሚጠቀልል አንድ መፈክር ያስፈልገናል - “ፍትህ ለኢትዮጵያ!”
ለምንፍትህ ለኢትዮጵያ!”?
ከፍ ብዬ እንደገለጽኩት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት (በተለይም 1966 አብዮት ማግሥት አንስቶ) ከፍ ያለ የፍትህ እጦት ከዳር እስከ ዳር ያስተናገደች አገር ናት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውና አሁንም ሙሉ በሙሉ ያልጠፋው የፍትህ እጦት ዘር፣ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ የኑሮ ደረጃ፣ሳይለይ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ላይ የጭካኔ በትሩን ያሳረፈና እያሳረፈ ያለ ክፉ ጠላታችን ነው፡፡ በዚህ ምክንያትም ይመስለኛል፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያንእገሌ ከእገሌሳይባል፣ ደረጃው ቢለያይም እንኳ ስለ ፍትህና ርትዕ መጓደልና አለመኖር የምናማርረው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ በሚገባ የተበየነበት አንድም ክልል የለም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ርትዕ ለሁሉም በእኩል መጠን የሆነለት አንድም ማኅበረሰብ የለም፡፡ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው እንዲሁም በማኅበራዊው ዘርፍ፣የምፈልገውንና የሚገባኝን ሁሉ በሥርዓት አግኝቻለሁየሚል የማኅበረሰብ ክፍል ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ ሁሉምጎደለብኝ፣ ቀረኝ፣ አነሰኝየሚል ቅሬታ አለው፡፡ ይህንን ስናይ፣ ፍትህ የተጓደለው፤ለአንድ ወይም ለተወሰኑ አካባቢዎችና ማኅበረሰቦች ብቻ ሳይሆን፣ ለመላዋ ኢትዮጵያ ነው፤ ብለን እንድናምን ያስገድደናል፡፡ 
የአገር ፍትህ ማጣት የሁላችንም ፍትህ ማጣት ነው፣ የአገር ርዕት-አልባ መሆን የሁላችንም ርዕት-አልባነት ነው፡፡ በአንደኛው ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ፣ ወይም ጎጥ የሚታይ የፍትህ እጦት፣ ይዘገይ እንደሆን እንጂ በሁላችንም ቤት መግባቱ አይቀርም፡፡ ይህን ማስቀረት የሚቻለው አገር በሁሉም መስክ ፍትህ በሚገባ ሲበየንባት ብቻ ነው፡፡
ስላጣነው ፍትህና ርትዕ በያለንበት መጮኻችን አግባብ ነው፣ ነገር ግን የፍትህ እጦቱ በተለይ ባለፉት 27 ዓመታት እንደታዘብነው፣ ተቋማዊና አገር-አቀፋዊ መልክና ቅርጽ ያለው፣ አልፎ ተርፎም የፖለቲካ የበላይነት ማረጋገጫ እስከመሆን የደረሰ፣ በአንዳንድ መልኩም የመጨቆኛ መሣሪያ ለመሆን እንደበቃ ተበዳዩ ሕዝብ ሲናገር ይሰማል፡፡ ይህንን አገር-አቀፍ ችግር ለመዋጋት አገራዊ ፍትህ ወሳኝ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የየራሳችንን የፍትህ ጥያቄ ብቻ አስመልሰንሁሉም ጥሩ ነውብለን አርፈን ለመተኛት አንችልም፡፡ የሌላው ችግር በአንድ ወይም በሌላ መንገድ እኛው   መምጣቱ አይቀርም፡፡ ይህ እንዳይሆን፣ አገራዊ ፍትህ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋታል፡፡
ስለዚህ፤ የየቡድናችን፣ የየማኅበራችን፣ የየብሔረሰባችን፣ የየብሔራችን፣ የየክልላችን፣ፍትህ በማያዳግም መልኩ እንዲረጋገጥ፣ እስቲፍትህ ለኢትዮጵያ!” እንበል፡፡ አዎ፤ፍትህ ለኢትዮጵያ”!! 

No comments:

Post a Comment