ዛሬ ሁለት ተቃራኒ ስሜቶችን አስተናግደናል፤ ደስታ እና ሀዘን፡፡ ደስታው፣ በታሪካችን፣ ምናልባትም ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሕዝብ በራሱ ፈቃድ፣ ያለምንም ትዕዛዝ፣ ማስፈራሪያ እና አበል፣ መሪውን ከልቡ ለማመስገን አደባባይ የወጣበት ታሪካዊ ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ሀዘኑ ደግሞ፣ ይህንን ደስታ እና በሕዝቡ ዘንድ የተፈጠረ እውነተኛ የአንድነት እና የተስፋ መንፈስ ለማጨለም በእኩዮች የተፈጸመው የሽብር ጥቃት ነው፡፡
ዴሞክራሲ በተወደሰበት፣ አሁን እያየን እና እያጣጣምነው ያለውን ለውጥ እየመሩ ላሉት መሪዎቻችን ምስጋና ለማቅረብ በተጠራው ታላቅ እና ደማቅ ሰልፍ ላይ ተሳታፊ በመሆኔ በጣም ዕድለኛና ደስተኛ ነኝ፡፡ ስለዚህች ታሪካዊ ዕለት ብዙ ለማለት አስቤ የነበረ ቢሆንም፣ የተፈጠረው አሳዛኝ ሁኔታ ግን አሁን ላይ ይህንን ለማለት አላስቻለኝምና በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፡፡ ለአሁኑ ግን፣ ይህንን አሳፋሪ እና ሰይጣናዊ ድርጊት ለፈጸሙ እና ላስፈጸሙ አካላት ይህንን ማለት እፈልጋለሁ፡፡
እናንተ የዚህ ድርጊት ፈጻሚና አስፈጻሚዎች፣ ማንም ሁኑ ምን፣ ጠ/ሚኒስትር አብይ እንዳሉት እኩይ ዓላማችሁ “ትናንትም አልተሳካም፣ ዛሬም አልተሳካም፣ ነገም አይሳካም!” ዓላማችሁ ምን እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፤ በአጭር ጊዜ ዕቅዳችሁ፣ የአሁኑን የለውጥ ጉዞ ለማደናቀፍ፣ በረዥም ጊዜ ደግሞ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ፡፡ ለዚህም ባለፉት ወራት ብዙ ጮኻችኋል፣ ብዙ ሞክራችኋል፡፡አንድ ነገር እወቁ፤ ኢትዮጵያ፣ እንደ ኢያሪኮ በጩኸት የምትፈርስ፣ እንደ ሰዶምና ገሞራ በእሳት የምትጠፋ አገር አይደለችም፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ ድረስ ከነችግሮቿም ቢሆን ጸንታ የኖረችው በመስዕዋትነት ነው፡፡ ለዛሬውም የለውጥ እና የአንድነት መንፈስ ዕውን መሆን ብዙ መስዕዋትነት ተከፍሎበታል፡፡ የዛሬውም መስዕዋትነት፣ ዶ/ር ዐብይ እንዳሉት፣ የዚህ ለውጥ ማስቀጠያ ነው፡፡ ዛሬ ያጣናቸው እና የተጎዱብን ወገኖቻችን የከፈሉት መስዕዋትነት ይህንን ጉዞ ይበልጥ ያፋጥነዋል እንጂ አያቆመውም፡፡ ስለዚህ እርማችሁን አውጡ! ብትችሉ ለሕዝብ ፈቃድ ተገዙ፡፡ ለሕዝብ ፈቃድ መገዛት ወረታው ብዙ መሆኑን ዶ/ር ዐቢይ፣ አቶ ለማ እና አቶ ገዱ አሳይተውናልና ከእነርሱ ተማሩ፡፡ ማሸበር ውጤቱ መሳቀቅ ነውና ልቦናውን ሰጥቷችሁ ከአሸባሪነታችሁ ተመለሱ!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይባርክ!